እንኳን ወደ የመጓጓዣ ፍትኀዊ እኩልነት የስራ ቡድን (TEW) በደህና መጡ!
አማርኛ •繁体字•简体中文• ភាសាខ្មែរ • 한국어 • Oromiffa • af-Soomaali • Español • Tagalog • ትግርኛ • Tiếng việt • English
ስለ እኛ
የእኛ ስራ እያንዳንዱ ሰው ሁሉም ደህንነቱ የተጠበቀ እና በተመጣጣኝ ዋጋ የመጓጓዣ አገልግሎት እንዲያገኝ ማረጋገጥ ነው። እኛ በተለይ ከዚህ ቀደም በቂ ድጋፍ ያላገኙ ማህበረሰቦችን በመርዳት ላይ እናተኩራለን።
የትርጉም አገልግሎቶች
ማመልከቻዎችን ወይም የድጋፍ ደብዳቤዎችን ለመሙላት እና ለማስገባት የቋንቋ ተደራሽነት አገልግሎት የሚፈልጉ ግለሰቦች፣ የጥምረት ተቋሞች እና ማህበረሰብ መሠረት ያደረጉ ድርጅቶች ወደ transportationequity@seattle.gov ኢሜይል ማድረግ ወይም በ (206) 530-3260 መደወል ይችላሉ።
ማን ማመልከት ይችላል?
ልምድ ካልዎት እና በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ካለው ቡድን ጋር ተዛምዶ ኖሮአቸው የሚከተሉትን የሚያግዙ ክሆነ ማመልከት ይችላሉ:
- የጥቁር፣ የአገር ተወላጆች እና የቀለም ህዝቦች (BIPOC) ማህበረሰቦች
- ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ማህበረሰቦች
- አዲስ ሰፋሪዎች እና ስደተኞች
- አካል ጉዳተኝነት ያላቸው ሰዎች
- LGBTQIA+ ሰዎች
- በመኖሪያ ቤት አጥነት ደህንነት የጐደላቸው ሰዎች
- በሴትነት እና የሴት-ጾታ የሚለዩ ሰዎች
- ወጣቶች እና በዕድሜ ገፍተው ያሉ ሰዎች
- ቀደም ሲል በእስር ላይ የነበሩ ሰዎች
- ከፍተኛ መፈናቀል የሚያጋጥማቸው ሰፈሮች
ልዩ የመዳረሻ ፍላጎቶች ካሉኝ ምን አይነት እርዳታ ማግኘት እችላለሁ?
የእኛን ቡድኖች ፍላጎቶች ለማስተናገድ ሁሉንም ጥረት እናደርጋለን። የኛ ሰራተኞች ለእርስዎ የተለየ ፍላጎቶች መፍትሄዎችን ለማግኘት ከእርስዎ ጋር አብረው ይሰራሉ።
ክፍያ ይከፈለኝ ይሆን?
አዎ! በመጀመሪያዎቹ ሶስት የአቅጣጫ ማስያዣ ወራት በሰዓት $50 ዶላር ያገኛሉ። እርስዎ አንዴ የአቅጣጫ ማስያዣ ሂደቱን ካጠናቀቁ፣ በሰአት $75 ዶላር ያገኛሉ እና በዓመት እስከ $7,500 ዶላር ሊያገኙ ይችላሉ።
ምን አደርጋለሁ?
እርስዎ ለሦስት ዓመታት እንዲያገለግሉ ይጠበቃል፣ እና ከመጀመሪያው የእርስዎ የሥራ ክፍለ ዘመን በኋላ ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት ማራዘም ይችላሉ። ከ2-4 ስብሰባዎች ላይ ይገኛሉ (በአብዛኛው በዙም (Zoom) ላይ) እና በየወሩ ከ9-10 ሰአታት አካባቢ ይሰራሉ። በእነዚህ ስብሰባዎች ወቅት ከሌሎች የቡድን አባላት እና የከተማው ሰራተኞች ጋር አብረው ይሰራሉ።
የምርጫው ሂደት ምንድን ነው?
በምልመላ ሂደት ወቅት የTEW አባላት እና የሲያትል መጓጓዣ መምሪያ (SDOT) ሰራተኞች የቀረቡትን ማመልከቻዎች እና የድጋፍ ደብዳቤዎችን ይገመግማሉ። ከዚያ በኋላ ይህ ቡድን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እጩዎችን ይመርጣል። ከቃለ መጠይቁ በኋላ፣ ቡድኑ የመጨረሻውን ውሳኔ ያደርግ እና ውጤቱን እጩዎችን ያሳውቃል።
የመጓጓዣ ፍትኀዊ እኩልነት ማዕቀፍ (TEF) ምንድን ነው?
TEF የበለጠ ፍትሃዊ እኩልነት የመጓጓዣ ስርዓት እንዲኖር ለማረጋገጥ ከማህበረሰብ አባላት ጋር ያደረግነው እቅድ ነው። አሁን እኛ ይህንን እቅድ ወደ ተግባር ለመቀየር እየሰራን ነው።
ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ወይም ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ በ transportationequity@seattle.gov ለኛ ኢሜይል ለመላክ ነፃነት ይሰማዎ። ከእርስዎ ለመስማት በጉጉት እንጠብቃለን!